ዓድዋ በእጅጋየሁ ሽባባው ሙዚቃ ሲታወስ
የሰው ልጅ ክቡር፣
ሰው መሆን ክቡር፣
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር፣
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፣ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ፡፡
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነጻነት፣
ሰው ተከፎሎበታል ከደምና ከአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነጻነት ምድር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር ሀገሬ፣
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፡፡
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን፣
ደግሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን፡፡
ዓድዋ ዛሬ ናት ዓድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለዓድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነጻነት ላበቁን ወገኖች፣
የጥቁር ድል አምባ፣ ዓድዋ፣
አፍሪካ፣ እምዬ ኢትዮጵያ፣
ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ፡፡
እጅጋየሁ ሽባባው