“የምርጫዬ” መተግበሪያ አጠቃቀም …
- “ምርጫዬ” የተሰኘውን የመራጮች መመዝገቢያ መተግበሪያ ከPlay Store / APP Store በማውረድ በስልክዎ ላይ ይጫኑ፣
- በስልክዎ ላይ ከተጫኑ ዝርዝር መተግበሪያዎች ውስጥ “ምርጫዬ” የሚለውን መተግበሪያ ይክፈቱ፣
- በመቀጠልም ከተከፈተው የ“ምርጫዬ” መተግበሪያ ላይ የሚጠቀሙበትን ቋንቋ ይምረጡ፣
- ቋንቋ መርጠው ከገቡ በኋላ ከሚያገኟቸው ዝርዝሮች ውስጥ “የእርስዎን መገለጫ ይፍጠሩ” የሚለውን ይጫኑ፣
- በመቀጠል “በፋይዳ አማካኝነት ወደ መለያ” የሚለውን አማራጭ ይጫኑ፣
- የፋይዳ ገጹ ሲመጣልዎ ከፋይዳ መታወቂያዎት ላይ 16 አኅዝ ያለውን ቁጥር (FAN) ካስገቡ በኋላ በስልክዎ የሚላክልዎን ባለስድስት አኅዝ የአንድ ጊዜ ማረጋገጫ ቁጥር (OTP) ይሙሉ፣
- መረጃዎን ከፋይዳ ሲያገኙ “ይቀጥሉ” የሚለውን በመጫን መተግበሪያው የሚጠይቅዎትን ቀሪ መረጃ በማስገባት መስማማትዎን በሳጥኑ ውስጥ ምልክት ያድርጉ፣
- በመቀጠል ያስገቡትን መረጃ ወደ መተግበሪያው ለመላክ “አስገባ” የሚለውን በመጫን ከመተግበሪያው ቋሚ የመራጭነት መለያ ቁጥር ያገኛሉ፤ ይህ ሊይዙት የሚገባ ቋሚ የመራጭነት መለያ ቁጥርዎ ነው፣
- ያስታውሱ! ቋሚ የመራጭነት መለያ ቁጥር አገኙ ማለት ምዝገባዎ ተጠናቋል ማለት አይደለም “ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይመዝገቡ” የሚለውን መጫን ይኖርብዎታል፣
- በመቀጠልም በአድራሻዎ መሠረት ቅርብ የሆነ የምርጫ ጣቢያ ለመምረጥ የምርጫ ጣቢያ ዝርዝር ያገኛሉ፣
- ከሚያገኙት የምርጫ ጣቢያ ዝርዝሮች ውስጥ የሚቀርብዎን የምርጫ ጣቢያ በመምረጥ “ይመዝገቡ” የሚለውን ይጫናሉ፣
- በመረጡት ምርጫ ክልል በኗሪነት ያልዎትን ቆይታ በዓመት እና በወር ያስገባሉ። ያስገቡትን መረጃ ትክክለኛነት በማረጋገጥ በሳጥኑ ላይ ምልክት በማድረግ ያረጋግጡ የሚለውን በመጫን ለምርጫው እራስዎን ይመዘግባሉ፣
- በመቀጠል የመታወቂያዎን ዓይነት በመምረጥ የመረጡትን መታወቂያ ፊት እና ጀርባ ፎቶ ማንሣት እና ማያያዝ፣
- መቀጠል ለምርጫ ቀን ይዘው የሚመጡት ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የምርጫ ካርድ ከ48 ሰዓት በኋላ ከመተግበሪያው ያገኛሉ፣
- ምርጫ ካርድዎን አትመው ለመያዝ “ወደ ዋና ገጽ ይመለሱ” የሚለውን አማራጭ በመጫን ዋና ገጽ ላይ የሚገኘውን “ያትሙ” የሚለውን አማራጭ መጫን ይኖርብዎታል።