Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ ተሳትፈዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲንና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት÷ በእስልምና አስተምህሮ አብሮ መብላትና መረዳዳት ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው እሴት ነው ብለዋል።
ይህም ለሰው ልጅ ክብር መስጠትን፣ ርኅራኄን፣ የጋራ ደስታንና አብሮነትን በተግባር መተርጎም እንዳለብን የሚያሳይ ሕያው የሕይወት ስንቅ ነው ሲሉ አመልክተዋል።
የኢፍጣር መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያን የብዝኃነት ውበት፣ አብሮነትና አንድነት የሚያንጸባርቅ እንደሆነም አውስተዋል።
በኢኮኖሚው ዘርፍ የምናስመዘግበው ስኬት ትርጉም የሚኖረው ልክ እንደዛሬው የኢፍጣር መርሐ ግብር በታላቅ የፍቅርና የመተሳሰብ ሰንሰለት ተሳስረን ለትውልድ የምትተርፍ ጠንካራ ሀገርን በጋራ መገንባት ስንችል ብለዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ለሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የረመዳን ጾም እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡
በለይኩን ዓለም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.