ማንቼስተር ዩናይትድ አስቶን ቪላን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ አስቶን ቪላን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በሜዳው ኦልድ ትራፎርድ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ አስቶን ቪላን ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ፤ ካሴሚሮ፣ ኩንሃ እና ሴስኮ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
የአስቶን ቪላን ብቸኛ ግብ ባርክሌይ ከመረብ አሳርፏል።
በዚህም ማንቼስተር ዩናይትድ ነጥቡን 54 በማድረስ በሊጉ ያለውን 3ኛ ደረጃ አስጠብቋል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ እና ሊድስ ዩናይትድ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት እና ፉልሃም 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
የሊጉ ጨዋታ ምሽት 1፡30 ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ ሊቨርፑልን ቶተንሃም ሆትስፐርን በአንፊልድ ያስተናግዳል።