የሁለት ዋንጫዎች ተሸላሚዋ እየሩስ ብርሃኑ…
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የወሎ ዩኒቨርሲቲ ለ18ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 444 ተማሪዎችን አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 463 የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ÷ ተማሪ እየሩስ ብርሃኑ ከእነዚህ ተመራቂዎች ውስጥ አንዷ ናት።
የሁለት ዋንጫዎች ተሸላሚ መሆን የቻለችው ተመራቂዋ÷ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በአካውንቲንግና ፋይናንስ የትምህርት ክፍል 3 ነጥብ 97 በማምጣት ነው የማዕረግ ተመራቂ የሆነችው።
ተማሪ እየሩስ ለዚህ ስኬት ያበቃት ለትምህርት ያላት ቦታና ጥረቷ እንደሆነ በመግለጽ ወደፊትም ተጨማሪ ስኬቶችን ለማስመዝገብ እንደምትጥር ተናግራለች።
አባቷ የማጠናከሪያ ትምህርት በምትማርበት ወቅት ምሽት ላይ እየጠበቀ ወደ ቤት እንደሚያስገባት በመግለጽ፤ ለውጤታማነቷ የቤተሰቦቿ እገዛ እንዳልተለያት ጠቁማለች።
የተማሪዋ እናት አበራሽ እውነቱ በበኩላቸው÷ ለፍተው ጥረው ያስተማሯት ልጃቸው እዚህ በመድረሷ እጥፍ ድርብ ደስታ ተሰምቶኛል ነው ያሉት።
በከድር መሀመድ