Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ የአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና ጉባኤን እንድታስተናግድ ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ ከተማ 5ኛውን የአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና ዓለም አቀፍ ጉባኤ እንድታስተናግድ ተመርጣለች፡፡

የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ አሁንም ለዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ተመራጭ መዳረሻ ሆና ቀጥላለች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፥ መዲናዋ ባለፉት ጊዜያት ትላልቅ ሁነቶችን በማስተናገድ ያሳየችው ጠንካራ የመስተንግዶ አቅምና ኢትዮጵያዊ እንክብካቤ እውቅና እንድታገኝ አስችሏታል፡፡

በዚህም 5ኛውን የአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና ጉባኤ እንድታዘጋጅ በአፍሪካ ሲዲሲ መመረጧ ነው የተገለጸው፡፡

በመጪው መስከረም ወር በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከ30 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይካፈላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.