Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቴህራን ላይ ሊወስዱት የነበረው አደገኛ የአየር ላይ ድብደባ ለሁለት ሳምንት ተራዘመ።

ምክንያቱ ደግሞ ሀገራቱ የሁለት ሳምንታት የሁለትዮሽ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ነው።

ሆኖም ቴህራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በፍጥነትና ደህንነቱ በተሟላ ሁኔታ እንድትከፍት ቅድመ ሁኔታ ተቀምጧል።

ከስምምነቱ ጀርባ የፓኪስታን ሽምግልና መኖሩን ትራምፕ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው አስታውሰዋል።

የፊታችን አርብ በፓኪስታን ኢስላማባድ የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች ለውይይት ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል::

የሆርሙዝ ወሽመጥ በመከላከያ ሀይሏ አጃቢነት ክፍት እንደሚሆን ቴህራን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል እወቁ ብላለች::

የሰዓታት እድሜ ቀርቶት የነበረውና ዓለምን አስጨንቆ የነበረው ዋሽንግተን በቴህራን ላይ ልትፈጽመው ያቀደችው ከባድ ጥቃት ግን በእርግጥም አለመፈጸሙ ተረጋግጧል።

ሲ ኤን ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.