Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት ቄስ ደረጄ ጀንበሩ ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ቄስ ደረጄ ጀንበሩ በመልዕክታቸው÷ የትንሳኤ በዓል ጥላቻን በፍቅር እንዲሁም በቀልን በይቅርታ የምናሸንፍበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና የፍቅር ማዕድ በማጋራት ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍንና የሕዝቦች አንድነት እንዲጠናከር ሁሉም በቅንነትና በታማኝነት እንዲሰራም ጥሪ አቅርበዋል።

በየሻምበል ምህረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.