Fana: At a Speed of Life!

ዕድገታችን ተጠናክሮ እየቀጠለ ከምንጊዜውም በላይ ታላቅ የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)የምናስመዘግበው ዕድገት ተጠናክሮ እየቀጠለ ከምንጊዜውም በላይ ታላቅ የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም አሉ።
‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፥ ቀጣዩ የብርሃን ተስፋ! በሚል መሪ ሀሳብ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም ኢትዮጵያ በንፋስ ኃይል አማካኝነት ጨለማን ለመግፈፍ፣ ዐቅምን በለየ የቅድመ ጥናት እና ልዩ እቅድ ወደ ተግባር በመግባት ዛሬ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን እውን አድርጋለች ብለዋል።
ለዘመኑ የኃይል ዐቅም ተደማሪ የሆነውን ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ተገኝተን በኩራት እያስመረቅን፤ የተገኘው ውጤት መሰል ስራዎችን ለማበራከት የሚያተጋን ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።
ፕሮጀክቱ 100 ሜጋ ዋት ንጹህ የኃይል አቅርቦት በመጨመር ወደ ዘርፈ ብዙ እና ቀጣይነት ባለው የኃይል መጻዒ ዕጣ ፈንታ ለመገንባት የምናደርገውን ጉዞ ያጠናክረዋልም ነው ያሉት።
ይህም አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ አብነት ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።
በሁሉም ዘርፎች የምናስመዘግበው የኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ ተጠናክሮ እየቀጠለ፣ ይበልጥም እየለማ ይሄዳል ብለው ከምንጊዜውም በላይ ታላቅ የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ሲሉ አመልክተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.