Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) የምክክር ጉባዔ ሒደቱን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-


👉 ህዝቡ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያለው ተስፋ ትልቅ ነው። ተስፋው መብትን ማስከበር ነው፤ ለዘመናት ወደ ጭቅጭቅ አልፎ ተርፎም ወደ ግጭትና ጦርነት የወሰዱንን አጀንዳዎች በትክክል ተነጋግሮ አቅጣጫ አስቀምጦ ሁላችንም ወደ ሰላም እንድንመጣ ማስቻል ነው።

👉 የተመካካሪዎች ቁርጠኝነትና ሃላፊነት በጣም የሚገርም ነው፤ የሚጋጩ፣ ጽንፍ ሊይዙ የሚችሉ ሀሳቦችን እንኳን ይዘው መጥተው በተቻላቸው መጠን ወደ መሐል ለመምጣት እየሰሩ ይገኛሉ።

👉 ወደ መሐል የመምጣት ሂደት ከማንም በላይ ሀገራቸውን እንደሚያስቀድም ስለተገነዘቡ ከሁሉም በላይ ሀገራችንን ማስቅደም አለብን ብለው ተመካካሪዎች አምነዋል።

👉 መጀመሪያ አካባቢ አንዳንዱ የራሱን ጎሳ፣ ማንነትና ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ጥያቄ ብቻ ነበር ይዞ የመጣው አሁን ግን የምናየው በጋራ እንሰማ፣ በጋራ ማንነታችን ይከበር፣ በጋራ መብቶቻችን ይከበሩ በሚል በተወሰነ ደረጃ ወደመሐል መጥተናል።

👉 500 ተመካካሪዎች በጋራ የሚሰባሰቡበት ደረጃ ላይ በምንደርስበት ጊዜ ደግሞ የበለጠ ወደ መሐል እንመጣለን። በ500 ተመካካሪዎች መድረክ ጥያቄዎች ይነሳሉ፤ ስለዚህ በመቀራረብ ሂደት መስጠትና መቀበል መኖር አለበት። ይህንን ነው መርህ አድርገን የምንሄደው።

👉 የመጀመሪያዎቹ የ500ቹ ስብሰባ ቀናት ቀላል እንደማይሆኑ ይጠበቃል። ምክንያቱም በበዛን ቁጥር ሁላችንም የመናገርና የመደመጥ ፍላጎት አለን።

👉 500 ትልቅ ስብስብ ነውና እዚያ ስብስብ ላይ የተወሰኑ ተግዳሮቶች መኖራቸው አይቀርም። መኖርም ይገባቸዋል። ዞሮ ዞሮ ወደ አንድ እንሰባሰባለን።

👉 እዚህም እዚያ የሚነሱ ትንንሽ ጥያቄዎችን የምንረታቸው በብዙ እውነታዎች ነው። ትክክለኛውን ነገር ለህዝባችን ባቀረብን ቁጥር ነገሮች እየታወቁ ይሄዳሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.