Fana: At a Speed of Life!

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከስዊዲን የፍልሰተኞች ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከስዊዲን የፍልሰተኞች ጉዳይ ሚኒስትር ዮሐን ፎርሰል ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እና ስዊዲን ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸውና ሀገሪቱም በኢትዮጵያ ተቋማት ግንባታ ላይ ቁልፍ ሚና መጫወቷን አስታውሰዋል።

በዚህም የስዊዲን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተፈጠረውን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁለቱ ሀገራት በሰለጠነ የሰው ኃይል የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት ዘርፍ አብረው መሥራት በሚችሉበት አግባብ ላይም ምክክር ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.