Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ አሕጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳኤል ሙከራ…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ “ሳርማት” የተሰኘ የኒውክሌር አረር የሚሸከም አሕጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አድርጋለች።

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በወቅቱ እንዳሉት÷ ሩሲያ በዓለማችን እጅግ ኃይለኛ የተባለውን አሕጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳኤል ሙከራ በስኬት አካሂዳለች።

ሩሲያ ይህንን አዲስ የጦር መሣሪያ ያበለጸገችው አሜሪካ ከዓመታት በፊት ከሚሳኤል መከላከያ ስምምነት መውጣቷን ተከትሎ ለደኅንነቷ ስጋት በመፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚሳኤሉ እስከ 35 ሺህ ኪሎ ሜትር የመጓዝ አቅም ያለው ሲሆን÷ ማንኛውንም የጸረ ሚሳኤል መከላከያ ዘዴ ጥሶ ማለፍ እንደሚችል መገለጹን አልጀዚራ ዘግቧል።

ከሳርማት በተጨማሪ አቫንጋርድ የተሰኘው ከድምጽ ፍጥነት በ27 እጥፍ የሚፈጥን ሚሳኤል እና ኦሬሽኒክ የተባሉ ዘመናዊ መሣሪያዎች ወደ ስራ መግባታቸውን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

እነዚህ ርምጃዎች የዓለምን የኃይል ሚዛን ለመጠበቅና የሩሲያን ስትራቴጂካዊ ደኅንነት ለማረጋገጥ ያለሙ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.