Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከአሜሪካ ነዳጅ ለመግዛት ተስማምታለች – ዶናልድ ትራምፕ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና ከአሜሪካ ነዳጅ ለመግዛት እና የንግድ አጋር ለመሆን ተስማምታለች አሉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት በቤጂንግ ታሪካዊ ጉብኝት ካከናወኑ እና ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ጋር ስኬታማ ሲሉ የገለፁትን ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ጋር ያደረጉት ውይይት ስኬታማ፣ ታሪካዊ እና በዓለም ከፍተኛ እውቅናን ያገኘ ነው ብለዋል፡፡

የቻይና እና አሜሪካ የንግድ ግንኙነት፣ የነዳጅ ሽያጭ እንዲሁም የታይዋን እና ኢራን ጉዳይ በሁለቱ ቀናት ውይይት የተነሱ አጀንዳዎች እንደነበሩ ጠቅሰዋል፡፡

ቻይና የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲከፈት ትፈልጋለች ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ÷ ቻይና ከአሜሪካ ነዳጅ ለመግዛት እና ከዋሽንግተን ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር መስማማቷንም አስታውቀዋል፡፡

በምላሹ ቻይና ያቀረበቻቸው ፍላጎቶች ምን እንደሆኑ ግን ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከመናገር ተቆጥበዋል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.