ተቋርጦ የነበረው የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ግንባታ ዳግም ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ተቋርጦ የነበረው የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ግንባታ ዳግም ተጀምሯል።
392 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የባቡር መንገድ ፕሮጀክቱ 2007 ዓ.ም ተጀምሮ በ2012 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም በሰሜኑ ጦርነት በደረሰበት ውድመት እና ዘረፋ ምክንያት ፕሮጀክቱ ተስተጓጉሎ ቆይቷል።
የፕሮጀክቱ መጠናቀቅ የንግድ ሥርዓቱን በማሳለጥና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።
በፕሮጀክቱ ዳግም ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በአለባቸው አባተ