ብልጽግና ፓርቲ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሄደ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልጽግና ፓርቲ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብር አካሂዷል።
የፓርቲው የምርጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብር “በጸና እና በተደራጀ የሴቶች ድምጽ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እናሻግራለን” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡
የምረጡኝ ቅስቀሳው በደብረ ማርቆስ፣ ላሊበላ፣ ዱርቤቴ፣ ሸዋሮቢት፣ ደንበጫ፣ ደብረታቦር፣ ወረኢሉ፣ አዴት፣ ደብረሲና፣ ወረታ፣ አጣዬ፣ ግንደወይን እና ሌሎች ከተሞች መከናወኑ ተመልክቷል፡፡
በምርጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብሩ ላይ በየአካባቢዎቹ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አባላት እና ደጋፊዎች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ብልጽግና ፓርቲ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ የሚሠራ ሀገራዊ ፓርቲ መሆኑን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን ጽኑ አጋርነት በመግለጽ ÷ ፓርቲው የጀመራቸውን የልማት፣ የሰላምና የብልጽግና ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ሕጋዊ እና የጸና ሀገረ መንግሥት ለመመስረት ሴቶች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸውም በመርሐ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል፡፡