በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ የተመረቀው ግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ምን አይነት ሴራሚኮችን ያመርታል፡- On May 23, 2026 90 ፋብሪካው የተገነባው በግራንዴር ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ነው፣ መሰረት ልማቱ በ300 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን÷ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ የሴራሚክና የፖርሲሌን ንጣፎችን ያመርታል፣ ፋብሪካውን ከዕቅድ ጀምሮ እስከ መሬት ዝግጅት ብሎም ሙሉ ሥራ ማስጀመር የወሰደው ጊዜ ዘጠኝ ወራት ብቻ ነው፣ በአሁኑ ወቅት 60×60 የሴራሚክ ንጣፎችን በስፋት ማምረት ጀምሯል፣ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ የምርት ዓይነቶቹን በማስፋት የ80×80፣ 60×120፣ 70×140 እና 80×160 መጠን ያላቸውን የንጣፍ ዓይነቶች እንዲሁም የአውሮፓን የጥራት ደረጃ ያሟሉ የፖርሲሌን ምርቶችን ማቅረብ እንደሚጀምር ይጠበቃል፣ ፋብሪካው ከ2 ቢሊየን ብር በላይ መዋዕለ ነዋይ የወጣበት ሲሆን÷ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሽግግር ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ያመላከተ ክንውን ነው፣ ለፋብሪካው ምርት የሚያስፈልጉት ጥሬ ዕቃዎች 80 በመቶ የሚሆነው ከፋብሪካው በ100 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ይገኛል፣ የፋብሪካው መከፈት የውጭ ምርት ጥገኝነትን የሚቀንስ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችላትም ጭምር ነው፣ 90 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint