በወላይታ ዞን ዲንቱ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በወላይታ ዞን ዲንቱ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
አደጋው ከዲላ ወደ ሶዶ ሲጓዝ የነበረ ዶልፊን ተሽከርካሪ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሀዋሳ ሲጓዝ ከነበረ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡
በደረሰው አደጋም እስካሁን የዶልፊኑን አሽከርካሪ ጨምሮ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወልዴ ቢሊሶ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በስምንት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ነው የገለጹት፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች አቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ጠቁመው ÷ የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት ምርመራ መጀመሩን አመልክተዋል፡፡