Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የሚተጉ ወጣቶችን መመልከት በበለጠ ትጋት እንድንሰራ መነሳሳትን ይፈጥርልናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የሚተጉ ወጣቶችን መመልከት በበለጠ ትጋት እንድንሰራ ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥርልናል አሉ።

ከንቲባዋ ‘ትውልዱ ገብቶታል’ በሚል መሪ ሀሳብ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዛሬው የወጣቶች ድጋፍ እና ተነሳሽነት እጅግ አስደናቂ ነበር ብለዋል።

እኛ ለኢትዮጵያ ብልጽግና በትጋት ስንሰራ፤ ወጣቱ ደግሞ የዚህ ስራ ፍሬ ተቋዳሽ እና የሀገሪቱን ብልጽግና የሚያጣጥም ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ሀገራቸውን የሚወዱ እና ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የሚተጉ ወጣቶችን መመልከት እኛም በበለጠ ትጋት እንድንሰራ ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥርልናል ነው ያሉት።

ሰሞኑን አዶናይ ብርሃነን የመሳሰሉ ወጣቶች እንደነ ዲላን ፔጅ ያሉ ታዋቂ የአጫጭር ማህበራዊ ሚዲያ ዜና አቅራቢዎችን ወደ ሀገራችን በማምጣት የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ ለመገንባት እያከናወኑት ያለው ተግባር የሚበረታታ እና ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ገልጸው፤ ወጣቶቹን “በርቱ!” ልንላቸው ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.