Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለአፍሪካ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካ ቀንን በማስመልከት ለመላው አፍሪካውያን ወንድሞችና እህቶች ለአፍሪካ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ከ63 ዓመታት በፊት የአፍሪካ አባቶች አዲስ አበባ ላይ በመሰባሰብ ነፃ እና የተባበረች አህጉርን የመገንባት ታላቅ ህልም ማለማቸውን አስታውሰዋል።

ይህ የአንድነት ህልም ዛሬም ድረስ ሳይደበዝዝ በደማቅ ሁኔታ መቀጠሉን ገልጸው፥ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በአንድነት መንፈስ በጋራ ለመቆም ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

አህጉሪቱን ለማበልጸግ የሚከናወኑ ተግባራት ብዙ በመሆናቸው ከቃላት ወደ ተግባር መሸጋገር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

አህጉሪቱ ያላትን እምቅ አቅም በመጠቀም በአንድነት የላቀ ከፍታ ላይ እንደርሳለን ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.