ሀድያ ሆሳዕና እና ምድረ ገነት ሽረ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና እና ምድረ ገነት ሽረ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የሀድያ ሆሳዕናን ግብ እዮብ አለማየሁ ሲያስቆጥር ዳንኤል ዳርጌ ደግሞ የምድረ ገነት ሽረን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል በተመሳሳይ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከሸገር ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 7 ሰዓት ላይ መደረግ ጀምሮ 34ኛው ደቂቃ ላይ የተቋረጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ በነገው ዕለት 3 ሰዓት ከ30 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚደረግ አክሲዮን ማህበሩ አስታውቋል፡፡
በተመሳሳይ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ ሊደረግ የነበረው የወላይታ ድቻ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም የሚደረጉ የአዲስ አበባ ስታዲየም መርሐ ግብሮች በተያዘላቸው ሰዓት የቦታ ለውጥ ተደርጎባቸው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚካሄዱ ይሆናል፡፡