Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ተረከቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ወደ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ሙሉ በሙሉ ተደራሽ መደረጉ ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታጠቅ ተፈራ እንዳሉት÷ ከትላንት ጀምሮ በክልሉ ሰፊ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ሲከናወን ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት የምርጫ ቁሳቁስ በክልሉ በሚገኙ በሁሉም የምርጫ ክልሎችና የምርጫ ጣቢያዎች ላይ በአግባቡ መድረሳቸውን ነው ያረጋገጡት፡፡

የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ሂደቱን ያለምንም መስተጓጎል እና ፍፁም በተሳለጠ መንገድ ማከናወን መቻሉን ለኢቢሲ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.