በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ እስካሁን ከ700 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዘንድሮው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በእስካሁኑ ሂደት ከ700 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል አሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፡፡
ሚኒስትሯ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ÷ በዛሬው ዕለት በተካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሃ ግብር እስካሁን 22 ነጥብ 2 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው ተሳትፈዋል፡፡
በዚህም እስካሁን ከ700 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላታቸው ገልጸው÷ ይህም 256 ሺህ ሄክታር መሬት የሚሸፍን መሆኑን አመልክተዋል፡፡