የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተለያየ ውሳኔ አሳለፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ምክር ቤቱ በቀዳሚነት የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስተዳደር ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ረቂቅ ደንቡ ተፈፃሚ እንዲሆን ወስኗል።
በመቀጠል የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ረቂቅ ደንቡን አፅድቋል።
በመጨረሻም በግል ዘርፍ ለህክምና ተቋማት ግንባታ እና ማስፋፊያ የሚውል መሬት ለማስተላለፍ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ተፈፃሚ እንዲሆን መወሰኑን የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡