የምርጫ ውጤቶች ከምርጫ ጣቢያዎች ወደ ምርጫ ክልሎች ገብተዋል – ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤቶች ሙሉ በሙሉ ከምርጫ ጣቢያዎች ወደ ምርጫ ክልሎች ገብተዋል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ ድምፅ የተሰጠባቸው ወረቀቶች ወደ ማዕከል እየገቡ ነው።
ከ1 ሺህ 138 የምርጫ ክልሎች 825 የምርጫ ክልሎች እስካሁን ውጤት ይፋ ማድረጋቸውን አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የምርጫ ክልሎች አሁንም የማዳመርና የማጣራት ሥራ እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ