Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሕንድ ታሪክ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ መሪ በመሆናቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ÷ ውድ ታላቅ ወንድሜና ጓደኛዬ ናሬንድራ ሞዲ የዓለማችንን ትልቁንና እጅግ ንቁ የሆነውን የዴሞክራሲ ማሕበረሰብ ዘላቂ እምነት በማግኘት ሕንድን በራዕይና በቁርጠኝነት በተከታታይ 3 የዴሞክራሲያዊ የስልጣን ዘመናት በመምራት ላስመዘገቡት ታሪካዊ ስኬት የተሰማኝን ደስታ እገልጻለሁ ብለዋል።

አስተዳደራቸው ሚሊየኖችን ከድህነት ያወጣ፣ ዲጂታል የሕዝብ መሠረተ ልማቶችን በሕዝብ ብዛት ልክ የዘረጋ እና ታይቶ የማይታወቅ የመሰረተ ልማት እድገት በማስመዝገብ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ያስገኘ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ናሬንድራ ሞዲ በ”ግሎባል ሳውዝ” በጥንካሬ እና በማያቋርጥ ሁኔታ ድምጽ በመሆን እንዳገለገሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው አውስተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.