Fana: At a Speed of Life!

በአዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር የሚኖሩ ጠቀሜታዎች…

👉 ለእያንዳንዱ የተመዘገበ ተሽከርካሪ ልዩ የሆነ የፊደል ቁጥር መለያና ስቲከር ለመስጠት፤

👉 ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መነሻ በማድረግ በደረጃ በመጠንና በንድፍ ወጥነት እንዲኖረው ማድረግ፤ ለዚህም በቬይና ስምምነት የተሰጠን ኮድ “ETH” ማካተት መቻሉ፤

👉 ቀደም ሲል የነበረው የተሽከርካሪ ምዝገባ እና ሰነዶች ህጋዊነት በማረጋገጥ ድጋሚ ለመመዝገብ፤

👉 በግልጽ የሚታይ እና በተለያዩ የብርሃን ሁኔታዎች ውስጥ በግልጽነት የሚታይ እንዲሆን አንጸባራቂ ምልክቶቹን ማካተት መቻሉ፤

👉 በግልጽ የሚነበብ ሕብረተሰቡ የሚያነበው እና ሕግ አስከባሪዎች ብቻ የሚያነቡት በግልጽ የፊደሎች አቀማመጦች እንዲኖሩት መቻሉ፤

👉 ፎርጀሪን (ማጭበርበርን) ለመከላከል እንደ ሆሎግራም፣ የውሃ ምልክት እና ማይክሮ ጽሑፍ ያሉ የደኅንነት ባህሪያት እንዲካተት መደረጉ፤

👉 በቀላሉ ከሲስተሞች (ከዲጂታል) ጋር ተነባቢ እንዲሆኑ እንደ ባርኮድ፣ QR ኮድ ወይም RFID ቺፖችን ለአስተማማኝ ዲጂታል መዝገቦች እና ክትትል መጠቀም መቻሉ፤

👉 ለከባድ የአየር ሁኔታን መቋቋም የሚችሉ ዘላቂ ቁስን መጠቀም መቻሉ፤

👉 ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ወጪ የሚቆጥብ መሆኑ፤

👉 ተሽከርካሪው ተመዝግቦ እስኪወገድ ድረስ በአንድ ሰሌዳ እና የፊት ለፊት መስታወት (Windshield) የሚለጠፍ ስቲክር የሚኖረው ይሆናል፡፡

👉 አዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ (ታርጋ) ለውጥ ተመሳሳይ ታርጋዎችን ለማስቀረት፣ ህገ ወጥ ታርጋን ለመከላከል፣ ከተሽከርካሪ ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል፣ የተሽከርካሪ ስርቆትን ለማስቀረት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት በመሆኑ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ጠቀሜታ እንዳለው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.