ተሰሚነታችን …
የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ “ቅድሚያ ለጎረቤት” የሚል ጥልቅ ወንድማማችነትን ያነገበ ሲሆን፣ በቀጣናዊ ትስስርና በፓን አፍሪካኒዝም እሴቶች ላይ የቆመ መርህ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
መሠረታዊ ዓላማውም የዜጎችን ሁለንተናዊ ክብር ማስጠበቅና የጋራ ብሔራዊ ጥቅም ማረጋገጥ ነው።
ኢትዮጵያ ለሀገራዊ ችግሮች ሀገር በቀል የመፍትሄ እሳቤዎችን፤ ከሩቅ ርዕዮተ ዓለም ርዕዮተ ኢትዮጵያን ታስቀድማለች፡፡
“ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” የሚል ብሂልም መከተል ጀምራለች፡፡
ይህ መርህ ኢትዮጵያ ከአህጉራዊ ወንድሞቿ ጋር በመተባበርና በመደጋገፍ የጋራ ብልጽግናን ለመገንባት ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል፡፡
የዲፕሎማሲ እሳቤዋ ከመንግሥታዊ ግንኙነት ባለፈ፣ በሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር የሚያጠናክርና ለሰው ልጅ ክብር ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ልብይሏል፡፡
መንግሥት በዓለም አቀፍ መድረክ ያለውን አስተማማኝ ተጽዕኖ የማሳደር አቅም ከሀገራዊ ተጨባጭ ጥንካሬዎች ጋር በማቀናጀት ስትራቴጂያዊ የበላይነትን እየፈጠረ ይገኛል ።
ይህም በሐሳብ የበላይነትና በአሸናፊነት መንፈስ ላይ የተገነባ ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነትን ፈጥሯል፡፡
ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መድረኮች በሰራቻቸው ስራዎች፣ ሀገራችን በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነቷ ከፍ እንዲል፣ ክብሯ እንዲጠበቅ፣ የራሷን ፍላጎት በብቃት የምታስከብርና በጎ ተጽዕኖ የምታሳርፍ ሀገር እንድትሆን አድርጓታል፡፡
ዲፕሎማሲ ሀገራዊ ክብርንና ጥቅምን ለማስጠበቅ የሚረዳ እሳቤና ተግባር እስከሆነ ድረስ፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ አይደለም፡፡
ስለሆነም መንግሥትና ህዝብ ይህን አቅም ይበልጥ በማጠናከር፣ ዜጋ ተኮር የሆነውን የውጭ ግንኙነትና የሀገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ሥራ አጠናክሮ መቀጠል ይገባል፡፡