Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የፓንደሚክ ፈንድ የቦርድ ተባባሪ ሊቀመንበርነትን ከሩዋንዳ ተረከበች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የፓንደሚክ ፈንድ የበላይ ቦርድ ተባባሪ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

ይህን ተከትሎም ዶ/ር መቅደስ ዳባ የፓንደሚክ ፈንድ የቦርድ ተባባሪ ሊቀመንበርነትን ከሩዋንዳ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሳቢን ንሳንዚማና ተረክበዋል፡፡

ዶ/ር መቅደስ በዚህ ወቅት ÷ የሕብረተሰቡን ሕይወት መታደግ የሚችልና የዓለምን የጤና ደህንነት ዋስትናን የሚያረጋግጥ ጠንካራ የጤና ሥርዓት በመገንባት ለትውልድ ማስተላለፍ አለብን ብለዋል።

ፓንደሚክ ፈንድ በበኩሉ ÷ በአዲሱ ኃላፊነታቸው ዓለም አቀፍ አጋርነቶች እንዲጠናክሩና ሀገራት ወረርሽኞችን ለመከላከል ለሚያደርጉት ኢንቨስትመንት የሚሰጠውን ድጋፍ በበላይነት በመምራት ለውጥ እንደሚያመጡ ያለውን እምነት ገልጿል፡፡

ፓንደሚክ ፈንድ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራትን አቅም በመገንባት ድንገተኛ የጤና አደጋ ክስተቶችን ለመከላከል፣ ለመለየትና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የተቋቋመ ዘርፈ ብዙ የፋይናንሲንግ አሰራር ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.