የዓለም ዋንጫው የምድብ 2ኛ ጨዋታዎች…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ 2ኛ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡
በምድብ አራት የምትገኘው አዘጋጇ ሀገር አሜሪካ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ከአውስትራሊያ ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡
በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ አሜሪካ ፓራጓይን እንዲሁም አውስትራሊያ ቱርክዬን በማሸነፍ በግብ ክፍያ ተበላልጠው በምድቡ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
በዚሁ ምድብ በመጀመሪያ ጨዋታዎቻቸው ሽንፈት ያስተናገዱት ቱርክዬ እና ፓራጓይ የመጀመሪያ ነጥባቸውን ለማሳካት ነገ ማለዳ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በሌሎች የምድብ 2ኛ ጨዋታዎች ምድብ ሦስትን እየመራች የምትገኘው ስኮትላንድ ከሞሮኮ ዛሬ ሌሊት 7 ሰዓት ሲገናኙ፥ በዚሁ ምድብ ብራዚል የመጀመሪያ ድሏን ለማሳካት ሌሊት 9 ሰዓት ከ30 ሄይቲን ትገጥማለች፡፡