Fana: At a Speed of Life!

አርሲ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 355 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሲ ዩኒቨርሲቲ በአምስት የጤና ሳይንስ ኮሌጆች እና በህግ ትምህርት ክፍል ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 355 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በድምቀት እያስመረቀ ይገኛል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳን (ዶ/ር) ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት ያስመረቃቸው ተማሪዎች በጤና ሳይንስ እና በህግ ትምህርት ዘርፎች የሰለጠኑ ሲሆን በኢትዮጵያ የጤና እና የፍትህ ዘርፍ የድርሻቸውን እንዲወጡ ይጠበቃል።

በሊያ ዱጉማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.