Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሻሻሉ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅ እና የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የማሻሻያ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የ2018 በጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት አዳምጧል።

እንዲሁም የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመረጃ ነፃነት አዋጅን አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አጽድቋል።

የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቱ አለነ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ረቂቅ አዋጁ የዜጎችን መረጃ የመጠየቅና ማግኘት መብት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋ።

አዋጁ አለም አቀፍ መብቶችን በመጠበቅ ፈጣን ቀልጣፋና ወቅቱ የጠበቀ መረጃ ፍሰት የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅሰዋል።

እንዲሁም የሀገራችንን ብሄራዊ ደህንነት በሚያረጋግጥ መልኩ የተዘጋጀ በመሆኑ ምክር ቤቱ እንዲያጸድቀው ጠይቀዋል።

ይህን ተከትሎም አዋጅ ቁጥር 1427/2018 ሆኖ ተሻሽሎ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፓርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን አፅድቋል።

የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እፀገነት መንግስቱ ÷ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያን የፍትህ ሥርዓት በማሻሻል ረገድ እጅግ የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል።

የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ለማቋቋም፣ የፍርድ ቤቶችን የሥራ ተደራሽነት ይበልጥ ለማስፋት እንደሚረዳም ጠቁመዋል።

በዚህም አዋጅ ቁጥር 18/2018 ሆኖ ተሻሽሎ በሙሉ ድምፅ መጽደቁን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.