Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ ነው – አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

አዲሰ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ.ኤም.ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ከመቋቋምን ጀምሮ በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ ነው አሉ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ አመራሮችና የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡

አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በወቅቱ እንዳሉት፤ በአሁኑ ወቅት የዓለም ተግዳሮት እየሆነ የመጣውን የአየር ንብረት መዛባት ኢትዮጵያ አስቀድማ በመረዳት መፍትሔ ለመሻት ውጤታማ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በመቅረጽ በቁርጠኝነት እየሠራች ትገኛለች።

መርሐ ግብሩ የደን ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ ማድረጉን ገልጸው፤ ይህንን ስኬት አጠናክሮ ለማስቀጠል መላው ሕዝብ በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ በነቃ ሁኔታ በመሳተፍ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ምክር ቤቱ በየዓመቱ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን በስፋት ሲያከናውን መቆየቱን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ በመርሐ ግብሩ በዓለም ደረጃ አስደናቂ ታሪክ እየሠራች መሆኑን ጠቅሰው፤ ልማቱ የደን ሽፋኑን ከማሳደግ ባለፈ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ በኩል ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አንስተዋል።

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በይፋ መተግበር መጀመሯ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.