Fana: At a Speed of Life!

ከ20 ሚሊየን በላይ ሰዎች የሚታደሙበት የአያቶላህ አሊ ኻሚኒ ስርዓተ ቀብር…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢራን የቀድሞ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ ስርዓተ ቀብር ከነገ ጀምሮ ለስድስት ቀናት ይካሄዳል፡፡

በቀብር ስነስርዓቱ ላይ ከ20 ሚሊየን በላይ ሰዎች እንዲሁም ከ100 በላይ ሀገራት ተወካዮች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቴህራን በዚህ ሁነት ላይ ከአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የሚቃጣ ከሆነ አጸፋው ከባድ ይሆናል በማለት አስጠንቅቃለች፡፡

አያቶላህ አሊ ኻሚኒ እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ በከፈቱት ጦርነት ባለፈው የካቲት ወር እስከተገደሉበት ጊዜ ድረስ ለ36 ዓመታት ሀገሪቱን መርተዋል፡፡

አሜሪካ እና እስራኤል በዚህ ወቅት በኢራን ላይ ጥቃት ለመፈጸም ከሞከሩ የከፋ አጸፋ ይጠብቃቸዋል ሲሉ የሀገሪቱ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ ከፍተኛ አዛዥ አሊ አብዱላሂ ዝተዋል፡፡

በሌላ በኩል አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና እውነተኛ ሰላምና ደህንነት እንዳይሰፍን ያላትን ንቀት በተደጋጋሚ አሳይታለች ኢራን ወቀሳ አቅርባለች፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኤስማኤል ባጋይ ጎረቤቶቻችን አሜሪካ እና እስራኤል በእኛ ላይ ከከፈቱት ጦርነት ትምህርት ሊወስዱ ይገባል ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በእመቤት ሲሳይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.