Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በኋላ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ በኋላ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቆይታችንን ተከትሎ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነናል ብለዋል።

በዚህ የአረንጓዴ ዐሻራ ወቅት ተስፋን መትከላችንን እንቀጥላለን ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዛሬው የምክር ቤቱ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.