Fana: At a Speed of Life!

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ይ ላቭሮቭ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው በሁለቱ ሀገራት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን፥ በወቅታዊ ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው የሚኒስትሮቹን ውይይት አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት፥ ውይይቱ የሀገራቱን ረጅም ዓመት ያስቆጠረ ታሪካዊ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ለማጠናከር ያለመ ነው።

ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ እንደ ብሪክስ ባሉ የባለብዙ ወገን መድረኮች ትብብራቸውን ይበልጥ አጠናክረው ለመቀጠል መስማማታቸውን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

በአንዱዓለም ተስፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.