ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ለቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አቀባበል አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ አቀባበል አድርገዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል።
በታላቅ የለውጥ ጉዞ ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የሚኖርዎት ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ ሲሉም ገልጸዋል፡፡