ለሱዳኑ ጦርነት አፍሪካዊ መፍትሔ ለማፈላለግ እየሰራሁ ነው – ኢጋድ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ለሱዳኑ ጦርነት አፍሪካዊ መፍትሔ ለማፈላለግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት ጋር እየሰራሁ ነው አለ፡፡
ኢጋድ በሱዳን ጉዳይ የሚመክረውን ሦስተኛ ዙር የልዩ መልዕክተኞች ስብሰባ በኬንያ ናይሮቢ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ በሱዳን ያለውን ቀውስ ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን፣ ትብብሮችና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ምክክር ተደርጓል፡፡
ውይይቱ በሀገሪቱ ያለው ቀውስ መፍትሔ እንዲያገኝ የቀጣናዊና የዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላትን ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ኢጋድ በሱዳን ያለውን ቀውስ በዘላቂነት ለመፍታት ከአባል ሀገራቱ፣ ከአፍሪካ ኅብረትና ከአውሮፓ ኅብረት እንዲሁም የሰላም ጥረት ከሚያደርጉ ሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራ አረጋግጧል፡፡
በሚኪያስ አየለ