Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ የጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አስተዳደር ላስመዘገበው ታሪካዊ ስኬት በኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ስም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለሁ ብለዋል።

በዘመናዊቷ ጣሊያን ሪፐብሊክ ታሪክ ውስጥ ወደር የሌለው የፖለቲካ መረጋጋት ማምጣት የቻሉ ጠንካራ እና ባለራዕይ መሪ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

የመሪዋ የማይናወጥ ቁርጠኝነትና ጥንካሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካቶችን የሚያነሳሳ ከመሆኑ ባሻገር በኢትዮጵያና በጣሊያን መካከል ያለውን ሁለገብ እና ጠንካራ አጋርነት ይበልጥ እያጠናከረው እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተውን የሁለቱ ሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት እናከብራለን ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.