Fana: At a Speed of Life!

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለዓለም ገበያ የሚበቁ የዲጂታል ምርቶችን አፍርቷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቻና (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ ለዓለም ገበያ የሚበቁ የዲጂታል ምርቶችን አፍርቷል አሉ፡፡
የኢንስቲትዩቱ የመጀመሪያ ዙር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስታርትአፕ ሠልጣኞች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት ተመርቀዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፤ ዛሬ የምንመለከታቸው ውጤቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሳኩት በልዩ ትጋት እና በመንግሥት ቁርጠኛ አመራር ምክንያት የመጡ ናቸው ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ ሲመሰረት ያነገባቸውን ራዕዮች በሚገባ እየተወጣና ስኬት እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግሥት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ያስቀመጣቸውን ግቦች እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቁርጠኛ አመራር ላይ በመመስረት ተቋም ከማደራጀት አንስቶ ከአጠቃላይ የሀገር ልማት ጋር ተመጋጋቢ የሆኑ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የውድድር ሂደቶችን አልፈው ላሸነፉ ሰልጣኞች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።
በለይኩን ዓለም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.