Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ የሚዳስስ መፅሀፍ  ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ የሚዳስሰው አዲስ መፅሀፍ  በዛሬው እለት ተመርቋል፡፡

መፅሀፉ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስራት ዓፀደወይን(ዶ/ር) የተፃፈ ሲሆን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያለፈባቸውን የታሪክ ውጣ ውረዶች እና ተቋማዊ የለውጥ ጉዞ በሰፊው የሚዳስስ ነው፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ አስራት ዓፀደወይን (ዶ/ር) ÷50 በመቶ የሚሆነው የመፅሀፋ የመጀመሪያ እትም ሽያጭ ለተቸገሩ ህፃናት ተማሪዎች የ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቁሳቁስ ሟሟያ እንደሚውል  ገልፀዋል።

የተቋማት ታሪክና ጉዞን መሰነድ የተሻለ ነገን ለመገንባት ወሳኝ ነው ያሉት ደራሲው÷መፅሐፉ ታትሞ ለምርቃት በመብቃቱ  መደሰታቸውን ገለፀው፣ለመፅሐፉ ህትመትና  ምርቃን አስተዋፅዎ ላበረከቱ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው በበኩላቸው ÷ መፅሐፉ ዩኒቨርስቲውን ማህበረሰብ  ብቻ ሳይሆን የከተማውን ማህበረሰብ ጉዞ ያመላከተ መሆኑን ተናግረዋል።

መፅሃፉን ላበረከቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስራት ዓፀደወይን(ዶ/ር) እና ቤተሰቦቻቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በነብዩ ዮሐንስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.