Fana: At a Speed of Life!

በመሰረተ ልማት ላይ የሚደርስን ጉዳት ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመሰረተ ልማት ላይ የሚደርስን ጉዳት ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል አለ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የመሰረተ ልማት ስርቆትና ውድመትን ለመከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የመሰረተ ልማት ሀብቶችን ማውደም የሀገርን የወደፊት ዕድገት ጥያቄ ውስጥ ይከታል፡፡

መንገድ፣ ድልድይ፣ መብራት፣ ውሃና ቴሌ ኮሙኒኬሽን ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት ብቻ ሳይሆን ለማህበራዊ አገልግሎት ወሳኝ መሆኑን አንስተው፤ እነዚህን መሰረተ ልማቶች ከስርቆትና ከውድመት መታደግ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ከመድረሱ በፊት መከላከል እጅግ ውጤታማ የሚያደርግ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

የህዝብ ንብረት የሆኑ መሰረተ ልማቶችን መጠበቅ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዜጎች መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት ሲፈጽምና ውድመት ሲደርስ ለሚመለከተው አካል በፍጥነት መረጃ በመስጠት የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በተካልኝ ሃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.