Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የኢንዱስትሪው ዘርፍ አበረታች ውጤት እያስመዘገበ ነው

የኢትዮጵያን ነባር ስኬቶች በማስቀጠል፣ ጉድለቶችን በመሙላት እና አዳዲስ የፈጠራ አቅጣጫዎችን በመከተል ሀገራዊ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎች በየዘርፉ እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
ሀገሪቱ ቀድሞ ስትከተል ከነበረው ግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ብዝኀ ዘርፍ ኢኮኖሚ ተሸጋግራለች፡፡
በዚህም ለኢንዱስትሪው ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት፣ ስኬቶች እየተመዘገቡ ነው።
የመደመር መንግሥት የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃት እና ምርታማነትን ለመጨመር በርካታ ስልታዊ እርምጃዎችን ወስዷል::
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን አቅም ለመገንባት፣ የውጭ ምንዛሪን ለመቆጠብ እና በገበያ ላይ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት የተጀመረው ሀገራዊ ንቅናቄ በርካታ ስራ ያቆሙ ፋብሪካዎች ወደ ማምረት እንዲመለሱ አድርጓል።
ቀደም ሲል የተገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የአሰራር ማነቆዎች በመቅረፍ፣ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ሰፊ እድል በመስጠት እና ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን አሳድጓል።
የኮንስትራክሽን እና የማዕድን ዘርፍን ለማነቃቃት በተሰራው ሥራ እንደ ሲሚንቶ፣ ብረታብረት እና የሀገር ውስጥ የቤት ቁሳቁስ አምራቾች የፖሊሲ እና የፋይናንስ ድጋፍ በማግኘታቸው አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ተደርጓል።
የኢንዱስትሪ ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በፈጠራ እና በዕውቀት ለመደገፍ የተሰሩ ስራዎች የአምራችነት ጥራትን እና ፍጥነትን አሻሽለዋል።
በአጠቃላይ የመደመር መንግሥት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያስመዘገባቸው ስኬቶች ሀገሪቱ በራሷ አቅም እንድትቆም እና የውጭ ጥገኝነትን እንድትቀንስ መሰረት ጥለዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ስልታዊ ንቅናቄ የዘርፉን ተወዳዳሪነት ከማሳደጉም በላይ ለሚሊየን ዜጎች ሰፊ የሥራ እድል ፈጥሯል፡፡
ይህንን የኢንዱስትሪ መነቃቃት አጠናክሮ በማስቀጠል የሀገሪቱን የረጅም ጊዜ የብልጽግና ጉዞ እውን ማድረግ ያስችላል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.