Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የባምባሲ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ከፈቱ

‎አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የባምባሲ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

‎የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ በክልሉ ቀደም ሲል ወደ ሥራ ከገቡት የቤጉ-መሶብ እና አሶሳ መሶብ አንድ ማዕከላት በተጨማሪ ሦስተኛው ማዕከል ሆኖ ሥራ ጀምሯል።

‎በክልሉ አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በተለያዩ ከተሞች የማስፋት ሥራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.