Fana: At a Speed of Life!

አረንጓዴ ዐሻራ የእርስ በርስ አብሮነትን ያጠናክራል – የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች

‎አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የእርስ በርስ አብሮነትን ያጠናክራል አሉ።
ነዋሪዎቹ አረንጓዴ ዐሻራ ኢትዮጵያ በዘርፉ ምሳሌ እንድትሆንና የፍራፍሬ ምርቶች በገበያው ላይ በብዛት እና በቀላሉ እንዲገኙ አስችሏል ብለዋል።
ችግኝ ከመትከል ባለፈም የተተከሉትን ችግኞች መንከባከብ እንደሚገባም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፤ መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያውያንን መልካም እሴትና ግንኙነት የሚያጠናክር ባህል በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ መርሐ ግብሩ ምቹ የሆነ ሃገርን ለትውልድ ማስረከብ እና ከተፈጥሮ ጋር የተስማማ ማህብረሰብ ለመፍጠር ያግዛል ነው ያሉት፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር መንግሥት ከተሞችን ማራኪና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ የያዘውን ኢኒሼቲቭ ለማሳካት የላቀ ሚና አለው ብለዋል።
በወርቅአፈራው ያለው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.