ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድለት የማይገባ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድለት የማይገባ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች በዚህ የክረምት ወቅት በነጻ በቀረበው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ የስልጠና መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድለት የማይገባ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል፡፡
የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኮርሶች በነጻ የሚገኙ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የሚሰጠው የምስክር ወረቀትም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ቀድመው መወሰናቸውን ጠቅሰው፤ አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው ብለዋል፡፡
ወጣቶች በዚህ የስልጠና መርሐ ግብር ላይ ለመሳተፍ በ ethiocoders.et ላይ መመዝገብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡