አስተዳደሩ አዲሱን አመት አዲስ አበባን ”በአዲስ የተስፋ ብርሃን” በሚል መሪ ቃል ለመቀበል መዘጋጀቱ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲሱን አመት ”አዲስ አባን በአዲስ የተስፋ ብርሀን” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሀ-ግብሮች ለመቀበል መዘጋጀቱን ገልጿል።
በመርሀ ግብሩ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት ስያሜ ተሠጥቷቸው የተለያዩ በጎ ስራዎች ይከናወንባቸዋል ተብሏል።
በዚህም ጳጉሜን አንድ የይቅርታ ቀን፣ ጳጉሜን ሁለት የአብሮነት ቀን፣ ጳጉሜን ሶስት የአምባሳደርነት ቀን፣ ጳጉሜን አራት የምስጋና ቀን እንዲሁም ጳጉሜን አምስት የብሩህ ተስፋ ብርሃን ቀን ተብሎ ይከበራል ተብሏል፡፡
የከንቲባው ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተርያት ወይዘሮ አልፊያ ዩሱፍ በመርሀ ግብሮቹ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በትዕግስት አብርሃም