Fana: At a Speed of Life!

ምክክሩ ለዘመናት የቆየውን የውይይት፣ የመግባባትና የመተማመን ባህል ያጎለብታል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ለዘመናት የቆየውን የውይይት፣ የመግባባትና የመተማመን ባህል ለማጎልበት ወሳኝ ነው አሉ፡፡

የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ዋና አፈ ጉባኤዋ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሀገራዊ ምክክሩ የቆዩ ችግሮችን በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ያሰፍናል ብለዋል።

በተጨማሪም ለዘመናት የቆየውን የውይይት፣ የመግባባትና የመተማመን ባህል ለማጎልበት ወሳኝ ነው ብለዋል።

ምክክሩ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ማመልከታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ሂደት ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ በ4 ሺህ ተመካካሪዎች አማካኝነት እየመከረ መሆኑ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.