Fana: At a Speed of Life!

የምክክሩ የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦች ለሥራ ቡድኖች መቅረብ ጀመሩ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የምክክሩ የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦች ለሥራ ቡድኖች መቅረብ ጀምረዋል አለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፡፡

ከእያንዳንዱ የባለ 500 አባላት የሥራ ቡድን የተመረጡ 30 አባላት ከስልታዊ ቡድኖች የቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦችን ተቀናጅተው 500 አባላት ላሏቸው 8 የሥራ ቡድኖች ማቅረብ ጀምረዋል፡፡

የተጠናቀሩ የአጀንዳ ሃሳቦች ላይ የመወያየቱ ሒደት በመጪው ሰኞ የሚቀጥል መሆኑንም ኮሚሽኑ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

ይህ የምክክር ደረጃ አንድ አጀንዳ ላይ የሚወያዩ 500 ተመካካሪዎች በሚወያዩበት አጀንዳ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የመጨረሻ ምክረ ሃሳብ ለማቅረብ ሞቅ ያለ ውይይት የሚያደርጉበት መሆኑ ተመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.