የፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋና ላምሮት የባለተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር ምዕራፍ 23 የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጥሎ ይካሄዳል።
የሙዚቃ ባለሙያዎችን ፣የሙዚቃ ወዳጆችንና መድረክ ያጡ ባለተሰጥኦ ድምጻውያንን በአንድ ያገናኘው ፋና ላምሮት የባለተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር ያለማቋረጥ ለ7 ዓመታት ተጉዟል።
የፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ከምድብ ሁለት ሰባት ተወዳዳሪዎች ጋር ቀጥሎ ይካሄዳል።
በቅዳሜው የምዕራፍ 23 ውድድሩ የምድብ ሁለት ተወዳዳሪዎች ከዛየን ባንድ ጋር በሁለት ዙር
ሥራቸውን ያቀርባሉ።
የምዕራፍ 23 ውድድር ለ13 ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን ÷ በሙዚቃ ባለሙያዎችና በተመልካቾች የአጭር የጽሑፍ መልዕክት ይዳኛል።
ተወዳዳሪዎች በተለያዩ ሳምንታት በራሳቸው፣ በዳኞች እና በተመልካቾች የሙዚቃ ምርጫ ይወዳደራሉ። በምዕራፉ ፍጻሜ የሚቀሩ አራት ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።
ለፍጻሜ የሚደርሱ አራት ተወዳዳሪዎች በቅርቡ ወደሚካሄደው 6ኛው አሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል፡፡
ውድድሩን የፊታችን ቅዳሜ ከ6 ሰዓት ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን፣ በፋና+ እንዲሁም በሁሉም የፋና ዲጂታል አማራጮች በቀጥታ ሥርጭት ይከታተሉ፡፡
በለምለም ዮሐንስ