Fana: At a Speed of Life!

አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን ከአስቶንቪላ ለማስፈረም ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል እንግሊዛዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ኤዝሪ ኮንሳን ከአስቶንቪላ ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡

መድፈኞቹ የዊሊያም ሳሊባ እና ጁሪያን ቲምበርን ጉዳት ተከትሎ ኤዝሪ ኮንሳን ወደ ስብባቸው ለመቀላቀል መስማማታቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ተጫዋቹ በነገው ዕለት የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ኤዝሪ ኮንሳ በ2019/20 የውድድር ዓመት አስቶንቪላን የተቀላቀለ ሲሆን እስካሁን ድረስ ለቪላ 286 ጨዋታዎችን አድርጓል፡፡

ኮንሳ አሰቶንቪላ ቪላ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ እንዲያሳካ እና የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን እንዲያገኝ ትልቁን ሚና ተጫውቷል፡፡

አስቶንቪላ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ኮንሳን ጨምሮ ዩሪ ቴሌማንስ፣ ሞርጋን ሮጀርስ እና ሉካስ ዲኜን ለተለያዩ ክለቦች አሳልፎ ሰጥቷል፡፡

የአርጀንቲናዊው ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ የቪላ ቆይታ አጠራጣሪ መሆኑን ተከትሎ ጃፓናዊውን ግብ ጠባቂ ዛዮን ሱዙኪን በዛሬው ዕለት አስፈርሟል፡፡

በአብረሃም አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.